የ44ኛው ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሠሩ ልማቶችን ጎበኙ።

0 Comments
ከጥቅምት 4 እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የሰበካ ጉባኤ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በድምቀት መጠናቀቁን ተከትሎ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ዋና ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በከተማ አስተዳደሩ የተሠሩ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ለተሻለ ሥራ በመትጋት በአጭር ጊዜ የልማት ሥራ እንዴት እንደሚሠራ ትልቅ ልምድ የሚገኝበት መሆኑን በማሳሰብ በሰጡት መመሪያ ሰፊ ጉብኝት ተደርጓል፡፡
ጉብኝቱ ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ የተሠሩ የኮሪደር ልማትን የወንዝ ዳርቻዎች ልማትን ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ መናፈሻ ያለው 21 ኪሎ ሜትር እንዲሁም የኢትዮ ኮሪያ ፓርክንና የተሰሩትን እጅግ ድንቅ የኮንሶ የእርከን ሥራዎችን በአዲስ አበባ በማካተት በርካታ አስደማሚ የሆነ በአጭር ጊዜ በ9 ወር ውስጥ የተሠሩ ልማቶችን ለማየት ተችሏል፡፡
በጉብኙቱ ላይ የእርከኑ ሥራ ከኮንሶ በመጡ ከ800 በላይ የእርከን ሥራ ጠቢባን የተገነባ መሆኑም ተገልጿል።
በጉብኝቱ የተሳተፉት የጉባኤው ተሳታፊዎች በከተማ አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ የተሠራውንና የከተማውን ገጽታ የቀየረውን ሁሉንም ተጠቃሚ ያደረገ ልማት በማየታቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *