ስርአተ ቅዳሴ ያድምጡ

0 Comments

ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን ቃል ስንመለከት “ሥርዓት” ማለት አሠራር፣ አፈፃጸም ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን “ቅዳሴ” ደግሞ ምሥጋና ማለት ነው፤ ይኸውም ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ለእግዚአብሔር የሚቀርብምሥጋና ማለታችን ነው። እንግዲህ ቅዳሴ በሐዲስ ኪዳን የተጀመረው በቤተ ልሔም ሲሆን የጀመሩትም ሰማያውያን መላእክት ናቸው፤ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም በ፭ሺ ፭መቶ ዘመን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ያለው አምላካዊ የተስፋ ቃል ሲፈጸም ቤተ ልሔም በምትባል የዳዊት ከተማ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ” ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን፤ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ እያሉ ሰማያውያን መላእክት እንዳመሰገኑ በሉቃስ ወንጌል ምዕ. ፪ ቁ፥፲፬ ተጽፎ እናገኛለን።