የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና ከሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት ጋር በመተባበር በሕጻናትና ወጣቶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጠ።

0 Comments
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮለጅ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በሕጻናትና ወጣቶች ላይ በተለይም በሴቶች ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛት ለማስቀረት ለኮሌጁ ማኅበረሰብ እና ለደቀ መዛሙርት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል።
ሥልጠናው በሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት አስተባባሪነት እየተሰጠ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካ ቤንች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ; ፣ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ፣
ሊቀ ኀሩያን ሰርፀ አበበ የኮሌጁ ዲን ;መ/ር ይቅርባይ እንዳለ የሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት ዋና ሥራ አሥኪያጅ የኮሌጁ ሠራተኞችና ደቀመዛሙርት በተገኙበት ሥልጠናው ተሰጥቷል ።
በኩረ ሰላም ብርሃኑ ሻረው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ኮሌጁ በቀጣይም ለመምህራንን እና የኮሌጁ ደቀመዛሙርት በተለያዩ ጉዳዮች ሥልጠና ለመስጠት በሰፊው እየሠራ መሆኑን ገልጸው ለሥልጠናው ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመስግነዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *