ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም)የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍቷና የዕርገቷ መታሰቢያ ክብረ በዓል በዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በጀሞ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም እና ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ።በክብረ በዓሉ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/ ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማ (ዶ/ር) ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በርካታ ምእመናን በተገኙበት…
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ስድስተኛውን የእምነትና ሥርዓት ዓለም አቀፍ ምክክር መርሐ ግብር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ፓትርያርክ በተገኙበት በግብጽ አባ ቢሾይ ገዳም ማካሔድ ጀመረ። የስደስተኛው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት የእምነትና ሥርዓት ዓለም ዓቀፍ ምክክር ጉባኤ ዋና ርእሰ ጉዳይ “የሚታየው አንድነት አሁን የት ነው?” በሚል ሲሆን ክርስቲያናዊ ኅብረትን ለማጠናከር የታሰበ ነውም ተብሏል። በዚህ ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጠው ኢኩሜኒካል እንቅስቃሴ ምክክር መርሐ ግብር…
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ድርጅት (#EOTCTV) በሰጠው ዕለታዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፩፻፲፰ ዓ.ም ጉባኤውን በመቀጠል ከአጀንዳ ፯-፲፫ ባሉት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጿል ። ረዳት ፕሮፌሰር መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል የጥናትና ምርምር መምሪያ እና የቅዱስ ሲኖዶስ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ድርጅት ማብራሪያውን ሰጥተዋል ። ረዳት ፕሮፌሰር…
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤበአንድ ግለሰብ ተዘጋጅቶ ‹‹ ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ›› በሚል እየተሠራጨ ያለውን መጽሐፍ የተመለከቱ የታላቁ ደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳም መምህር የሆኑት መጋቤ ምሥጢር አባ ክንፈሚካኤል ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት መጽሐፉ እንዲመረመር ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት መጽሐፉ እንዲመረመር እና ያለበት ግድፈትና የስሕተት ትምህርት ተለይቶ እንዲቀርብ ወደ ሊቃውንት ጉባኤ የመራው ሲሆን፣ የሊቃውንት…
በ፭ኛው መ/ክ/ዘ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ዘጠኙ ቅዳሳን (ተሰዓቱ ቅዱሳን) አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም ጻድቁ ጥቅምት ፲፬ ቀን የተሰወሩበት ዕለት በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ አቡነ አረጋዊ በሀገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው "ንጉሥ ይስሐቅ" እና "ቅድስት እድና" ይባላሉ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው። ስማቸው…
1. የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እንዲመሩና እንዲይዙ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 2. የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የከሚሴ የደቡብ ወሎ ልዩ ዞን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ደርበው እንዲመሩ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 3. የምሥራቅ ወለጋንና የሆሮ ጉድሩን ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ…
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚገኙ መንፈሳዊ ኮሌጆች አንጋፋው የብዙ ሊቃውንት ማፍለቂያ የሆነው የስዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለመምህራን እና አስተዳደር ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል። ሥልጠናውን ከሰጡት መምህራን መካከል አንዱ ፕሮፈሰር አባ ኃይለገብርኤል ግርማ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ በማስተማር ሥነ ዘዴ ( Pedagogical Sciences ) የማስተማር ጽንሰ-ሐሳብ እና ልምምድ እንዲሁም ሥነ ዘዴዎችን ዙሪያ ሥልጠና ተሰጥተዋል ።…
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጣለችበትን ሓላፊነት ለመወጣት እና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በሃይማኖት፣ በምግባር እና በዕውቀት የሚያገለግሉ ደቀ መዛሙርትን እያፈራ የሚገኝ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ተቋም ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ይህንን ተልዕኮውን አጠናክሮ ለመቀጠል እያከናወነ ካለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል በመደበኛ እና በማታው ትምህርት መርሐ ግብር ከሚሰጠው የነገረ መለኮት ትምህርት በተጨማሪ ለመማር ፍላጎቱ እያላቸው የቦታ ርቀት ገድቧቸው ትምህርቱን መከታተል…
በየሳምንቱ እሑድ እሑድ ይቀደሳል። በየወሩ የቅዱስ ሚካኤል፣ የቅዱስ ገብርኤል፣ የቅድስት ድንግል ማርያምና የበዓለ እግዚአብሔር ይቀደሳል። በየዓመቱ ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል ሐምሌ ሥላሴ ነሐሴ 1-16 ጳጉሜን 3 ቅዱስ ሩፋኤል የዘመን መለወጫ መስከረም 1ቀን መስከረም 17 በዓለ መስቀል ኅዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል ታሕሣሥ 19 ቀን ቅዱስ ገብርኤል የልደት በዓል ጥር 11 ቀን በዓለ ጥምቀት የትንሣኤ ግንቦት 1 ቀን የልደታ ሰኔ 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ሀምሌ 5 አቦ ፡፡
Get in Touch 24/7
Square, Ain Aar, Lebanon
God is Good All The Time!
Subscribe to our News,