ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በወላይታ ከተማ የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከፈተ።

0 Comments
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጣለችበትን ሓላፊነት ለመወጣት እና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በሃይማኖት፣ በምግባር እና በዕውቀት የሚያገለግሉ ደቀ መዛሙርትን እያፈራ የሚገኝ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ተቋም ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ይህንን ተልዕኮውን አጠናክሮ ለመቀጠል እያከናወነ ካለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል በመደበኛ እና በማታው ትምህርት መርሐ ግብር ከሚሰጠው የነገረ መለኮት ትምህርት በተጨማሪ ለመማር ፍላጎቱ እያላቸው የቦታ ርቀት ገድቧቸው ትምህርቱን መከታተል ላልቻሉ የቤተ ክርስቲኒቱ አገልጋዮች እና ምእመናን የነገረ መለኮት ትምህርትን በርቀት የትምህርት የማስተማሪያ ሥርዓት ተደራሽ ለማድረግ ነው፡፡
በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው በርቀት እና በይነ መረብ ትምህርት ኮሌጅ በኩል በዋናው ግቢ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ቅርንጫፍ ማእከላት ተከፍተው ትምህርቱ በሁሉም አካባቢዎች እንዲስፋፋ ወስኗል።
በዚህም መሠረት የዩኒቨርሲቲው ርቀት እና በይነ መረብ ትምህርት ኮሌጅ የመጀመሪያውን የርቀት ትምህርት ቅርንጫፍ በወላይታ ሀገረ ስብከት በዛሬው ዕለት የከፈተ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ደግሞ ሁለተኛውን ቅርንጫፍ በጅማ ሀገረ ስብከት እንደሚከፍት ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
መረጃው ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *