ልዩ ልዩ ዜናዎች

19 Oct, 2025

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

• ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ • ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ ቅዱስ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፤ የጎደለብንን እየሞላ አገልግሎታችንን እያቃና ከዚህ ላደረሰን፣ ይህንን ዓመታዊና ሐዋርያዊ ጉባኤያችንን ለማካሄድም ለሰበሰበን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና እናቀርባለን፡፡ “ወእፌጽም ታሕጻጸ ሕማሙ ለክርስቶስ በሥጋየ በእንተ ሥጋሁ እንተ ይእቲ…

19 Oct, 2025

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሄዳል፡፡

የመጀመሪያው ጉባኤ ጥቅምት ፲፪ ቀን (የቅዱስ ማቴዎስ በዓል) ሲኾን፣ ሁለተኛው ደግሞ ርክበ ካህናት (በዓለ ትንሣኤ በዋለ በ፳፭ኛው ቀን፣ በበዓለ ሃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ የሚከበረው) ነው፡፡ /ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፭ ቁጥር ፻፷፬/፡፡ በዮሐንስ ወንጌል እንደተገለጸው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሣ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ ተገልጦ ከዐሥራ አንዱ ቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ምሳ በልቷል፡፡ ከምሳ በኋላም ጌታችን ቅዱስ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ጠርቶ ትወደኛለህን?…

8 Oct, 2025

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና ከሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት ጋር በመተባበር በሕጻናትና ወጣቶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮለጅ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በሕጻናትና ወጣቶች ላይ በተለይም በሴቶች ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛት ለማስቀረት ለኮሌጁ ማኅበረሰብ እና ለደቀ መዛሙርት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል። ሥልጠናው በሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት አስተባባሪነት እየተሰጠ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካ ቤንች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሰዋስወ…

8 Oct, 2025

የ44ኛው ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሠሩ ልማቶችን ጎበኙ።

ከጥቅምት 4 እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የሰበካ ጉባኤ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በድምቀት መጠናቀቁን ተከትሎ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ዋና ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በከተማ አስተዳደሩ የተሠሩ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ለተሻለ ሥራ በመትጋት በአጭር ጊዜ የልማት ሥራ እንዴት እንደሚሠራ ትልቅ ልምድ የሚገኝበት መሆኑን በማሳሰብ በሰጡት መመሪያ ሰፊ ጉብኝት ተደርጓል፡፡ ጉብኝቱ ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ የተሠሩ…