የደብረ ሲና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰ/ጉ/የሕግ ክፍል ሥራና ኃላፊነት ዝርዝር የሚያሳይ ሠንጠረዥ
| ተ.ቁ | የሥራው መደብ | የሥራ ዝርዝር | ምርመራ |
| 1 | የሕግ ክፍል ሥራና ኃላፊነት | በቅዱስ ሲኖዶስ የሚመጡ ሕጎች፣ ደንቦችና ድንጋጌዎች በመንበር ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚወሰኑ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ለሰበካው ጉባኤ ኃላፊዎችና በጠቅላላው ለካህናትና ለምእመናን በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት መሠረት ሕጋዊ መመሪያና መግለጫ እየሰጠ እንዲያውቁትና እንዲያጠኑት ያደርጋል፡፡ | |
| በአጥቢየው ሰበካ ውስጥ በካህናትም ሆነ በምእመናን መካከል የሚፈጠር አለመግባባት ቢኖር ወደ ክስ ደረጃ ሳይደርስ እርስ በእርስ በመተራረም በይቅርታና በዕርቅ እንዲወገድ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ | |||
| የክሱ አቤቱታ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ሆኖ ሲገኝ የከሳሹና የተከሳሹን የሕግ መብት በመጠበቅ የሁለቱንም ወገን ማስረጃዎች በጥንቃቄ ተመልክቶ በቃለ ዐዋዲው በአንቀጽ 63 መሠረት የውሳኔ ሐሳብ ለሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡ | |||
| በክብረ በዓል ቀን ከሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት በሚሰጠው መመሪያ መሠረት እንደ አስፈላጊነቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊና ሕዝባዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የበዓሉን ሥነ-ሥርዓት ያስከብራል፡፡ | |||
| ለምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት የማይጠቅሙና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የማይውሉ ሸቀጣ ሸቀጦች በቤተ ክርስቲን ቅጥር ውስጥ እንዳይሸጡና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት የሚቃረኑ ተግባራት እንዳይፈጸሙ ከስብከተ ወንጌል እና ከሰንበት ት/ቤት ክፍሎች ጋር በመሆን ይከላከላል፤ ሥነ ሥርዓቱንም ያስጠብቃል፡፡ | |||
| ማንኛውንም መንፈሳዊና ሥጋዊ ሕግ ነክ ጉዳዮችን ይከታተላል፤ ለቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደርም የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ | |||
| ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክሎ በማንኛውም የሕግ አካል ዘንድ ይከራከራል፡፡ |