በጎ አድራጎት ክፍል

የደብረ ሲና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰ/ጉ/የምግባረ ሠናይ(በጎ አድራጎት) ክፍል ሥራና ኃላፊነት ዝርዝር የሚያሳይ ሠንጠረዥ

ተ.ቁየሥራው መደብየሥራ ዝርዝርምርመራ
1የምግባረ ሠናይ/በጎ አድራጎት ክፍል ሥራይህ ክፍል በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙትን የሰንበቴ፣ የዕድር፣ የልዩ ልዩ ምግባረ ሠናይ ማኅበራትን እና በጎ አድራጊ ግለሰቦችን በማስተባበር አሳዳጊ ያጡ ሕፃናትን ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን አረጋውያንና ችግረኞችን ለመርዳት የሚያስችል ክፍል ነው፡፡ 
በአጥቢያው ሰበካ ያሉት ችግረኞች በተደራጀ አቋም የሚረዱበትንና ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ ለመፈለግ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር ለሚመለከተው ክፍል ያቀርባል፡፡ 
ለመሥራት ችሎታና ዕቅቀት ያላቸው ችግረኞችን መርጦ በራስ አገዝ የልማት መርሐ ግብር ሠርተው እንዲጠቀሙ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር በመነጋገርና በመጻጻፍ ሁኔታውን እየተከታተለ ያስፈጽማል፡፡ 
መንፈሳዊና ሥጋዊ አኗኗራቸው የተሻሻለ እንዲሆን ከካህናቱ መካከል በዕቅቀቱና በግብረ ገብነቱ የተሻለው ካህን ተመርቶ በተወሰነ ሰዓት እንዲያስተምራቸውና እንዲመክራቸው የትምህርት መርሐ ግብር ያዘጋጃል፡፡ 
በሰንበት፣ በወርና በዓበት በዓላት በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ በትምህርተ ወንጌል ሰዓትና ሌላውም መንፈሳዊ አገልግሎት ሲካሄድ በዓውደ ምሕረት እየተዘዋወሩ ድምጽ በማሰማት እንዲያስቸግሩ አመች በሆነ ቦታ በአንድነት አሰባስቦ ጸሎተ ቅዳሴና ትምህርተ ወንጌሉን እንዲከታተሉ ርዳታም ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ 
በአጥቢያው ሰበካ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወላጅ ወይም አሳዳጊ የሌላቸው ሕፃናት ጊዜያዊና ዘላቂ ርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ እያጠና ለሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በማቅረብ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡ 
ምእመናንን፣ በጎ አድራጊ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በማስተባበር ችግረኞች፣ ጧሪና ረዳት የሌላቸው ሽማግሌዎችና ባልቴቶች በቤተ ክርስቲያን አካባቢ መጠለያና ምግብ እንዲያገኙ ዐቅም በፈቀደ መጠን ያመቻቻል፤ ጤናቸውንም ይንከባከባል፡፡