የደብረ ሲና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰ/ጉ/የዕቅድና ልማት ክፍል ሥራ ዝርዝር የሚያሳይ ሠንጠረዥ
| ተ.ቁ | የሥራው መደብ | የሥራ ዝርዝር | ምርመራ |
| 1 | ዕቅድና ልማት ክፍል | የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊጊ ዕቅድ በማውጣት ልዩ ልዩ የሥራ ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ፤ የዕቃ፤ የዕውቀትና የጉልበት ርዳታና መዋጮ ከምእመናን፤ ከልዩ ልዩ ድርጅቶች ሊገኝ የሚችልበትን ሁኔታ እያጠና ለሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡ | |
| ለአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን የገቢ ምንጭ የሚገኝበትን ተስማሚ የሥራ መስክ ያዘጋጃል፤ ለንዋየ ቅድሳት፤ ለመጻሕፍት፤ ለአልባሳትና ለሌላም የቤተ ክርስቲን አገልግሎት የሚውልና ለገቢ ማስገኛ የሚሆን የቅርጻ ቅርጽና የተግባረ ዕድ ሥራ እንዲቋቋም ያስደርጋል፡፡ | |||
| በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን የሚገኙት ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችም ያላቸውን ዕውቀት፣ የጥሬ ገንዘብ ሀብት ልዩ ልዩ ዕቃዎችና የሰውን ጉልበት ጭምር በማስተባበር ለቤተ ክርስቲያኑ ልማት ሥራ እንዲውል ያስደርጋል፡፡ | |||
| ካህናት በትርፍ ጊዜያቸው ራሳቸውን ለመርዳት እንዲችሉ የገቢ ምንጭ ለማስገኘት የሚመለከታቸውን በማስተባበር ከቤተ ክርስቲያኑ አገልጋዮች መካከል እየሠለጠኑ በየዝንባሌያቸው እንዲሠማሩና የምርት ውጤት እንዲያስገኙ ያስደርጋል፡፡ | |||
| ከልማቱ የሚገኘው ገቢ በሰበካ ጉባኤው ካርኒ እየተሰበሰበና በገንዘብ ቤቱ እየተጠቃለለ በቤተ ክርስቲያኑ ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ገቢ ይሆናል፡፡ | |||
| የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ቦታዎች እንዲለሙ እያጠናና እያስጠና ተግባራዊ እንዲሆን ለሰበካ ጉባኤው ያቀርባል፡፡ | |||
| የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ የይዞታ ቦታዎች ከመመሪያ ውጭ የበላይ አካል ሳይፈቅድ ለሦስተኛ ወገን እንዳይሰጡ ይቆጣጠራል፤ ይከታተላል፡፡ | |||
| የሥራውንም ውጤት በሚመለከት በየሦስት ወር ለሰበካ ጉባኤው ሪፖርት ያቀርባል፡፡ |