የሰንበት ት/ቤት ክፍል

በሥርወ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት  የትምህርት ክፍሉ አገልግሎት

  1.  የመጀመሪያው የጎልማሶች መሠረተ ትምህርት  ነው  በዚህም   ክፍል ሁለት  አይነት አገልግሎት አለ የመጀመራያው  ፊደል ማስቆጠር ሁለተኛው ቃላት ምሥረታ  ይማራሉ በደንብ ማንበብ መጻፍ እስኪችሉ በዚህ ቆይተው ከዛ ወደ መደበኛው ኮርስ  ይዛወራሉ፡፡
  2.  አንድ ምእመን የሰንበት ት/ቤቱ አባል ለመሆን  የሚወስዳቸው መሠረታዊ  ኮርሶችን  ይሰጣል፡፡
  3. በሰንበት ት/ቤት ሕጻናት ክፍል ያሉ  የነሱን ወላጆቻቸውን    እያስተማረ ይገኛል፡፡
  4. አጠቃላይ  የሥ/ሃ/ሰ/ት/ቤት አባላትን   የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ  ያሰተምራል።

በሥ/ሃ/ሰ/ት/ቤት/ግንኙት  ክፍል የሚሠሩ የሥራ ዝርዝር

  • አዳዲስ አባላትን በመመዝገብና ፎርም በማስሞላት  ለ3 ወር ኮርስ ሰጥቶ ለትምህርት ክፍሉ ያስረክባል
  • በየጊዜው የሚደረጉ አገልግሎቱ በመቅረጽ ፋይል ያስቀምጣል እንዲሁም አገልግሎቱን  በሚድያ ተደራሽ ያደርጋል
  • ከትምህርት ክፍሉ ጋር በመሆን ኮርሰኞች የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት በማሟላት. ለምሳሴ  ጉርድ ፎቶ፣ የምስክር ወረቀት የመሳሰሉትን በማዘጋጀት ያስመርቃል
  •  በየጊዜው ለሚኖሩ በዓላት የፎቶና  የቪድዮ ማስታወቂያ ይሠራል
  •      የ፬ቱንም ምድብ በየዓመቱ ከመዝሙር ክፍሉ ጋር በመሆን. ምድብ በማሰባጠር ትልቁን ድርሻ ወስዶ ቡድን በመክፈት ፬ቱን ምድብ በየደረሳቸው  ክፍል በማስገባት ይቆጣጠራል
  • አድባራትን በሚያስፈልጋቸው አገልግሎት ያግዛል
  • አዳዲስ ወደ ክፍሉ ለሚገቡ አባላት ኮርስ ይሰጣል. ለምሳሌ. የኮምፒውተር ስልጠና. ፣የካሜራ፣የፕሪንተር ስልጠና ሰጥቶ ለአገልግሎት ብቁ ያደርጋል
  • አገልግሎታቸው ከዚህ ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ ለሚሳፈሩ የሚያስፈልጋቸውን መሸኛ ሰጥቶ በክብር ያሰናብታል
  • በዋነኝነት ሚድያውን ይቆጣጠራል
  • የሰንበት ት/ቤት አባልነት መታወቂያ ይሰራል
  • ጽሑፎችን የማስተካከል ሥራ፣ ኮፒ ፕሪንት በማድረግ ለየ ክፍላቱ አገልግሎት ይሰጣል።

የሥርወ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት የንብረት ክፍል የስራ ድርሻ

 በንብረት ክፍላችን ______አባላት በንዑስ ክፍልነት ያሉን ሲሆን የስራ ድርሻችንም እንደሚከተለው ነው:-

1. በንብረት ክፍል ስር የሚገኙ ንብረቶችን በተዘጋጀላቸው የንብረት ቅጽ ላይ መዝግቦ በመያዝ በአይነታቸው ለይቶ በአግባቡ መጠበቅ እንዲሁም ብልሽቶች እንዳይደርስባቸው መጠበቅ።

2. በተለያየ ግዜ በግዢም ሆነ በስጦታ ወደ ክፍሉ የሚገቡ አዳዲስ ንብረቶችን እየተረከበ በንብረት መረከቢያ ቅጽ ላይ በመመዝገብ በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ።

3. በክፍሉ ውስጥ ከሚገኙ ንብረቶች መካከል በውሰት የሚወጡና የማይወጡ ንብረቶችን ይለያል።

4. ለአገልግሎት በውሰት የሚወጡ ንብረቶችን የማዋሻ ቅፆችን በማዘጋጀት በቅፁ ላይ እየመዘገበ ይሰጣል ያውሳል። የተዋሱትን ንብረቶች በተፈቀደላቸው የግዜ ገደብ ውስጥ መመለሳቸውን ይከታተላል ያልተመለሱ እንዲመለሱ ያድርግልን

5. በተለያየ ሁኔታ ከክፍሉ የጓደሉ (የጠፉ) የተበላሹ የሚጠገኑበትን የሚተኩበትን መንገድ ያመቻቻል ለክፍሉ አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑ የመገልገያ መሳሪያዎች እንዲሟሉ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር የበኩሉን አስተዋፅኦ ያደርጋል።

6. በንብረት ክፍሉ ስር የሚገኙ ንብረቶችን የሰ/ት/ቤቱ መሆናቸውን የሚያመለክቱ መለያ ምልክት እንዲኖር ያደርጋል።

7. ቢበዛ ሁለቴ ካነሰ አንድ ግዜ በዓመት ውስጥ የየክፍሉን ንብረቶች ቆጠራ ያከናውናል።

8. በተለያየ ግዜ በስጦታም ሆነ በማንኛውም መንገድ ወደ ሰ/ት/ቤታችን የገባውን ንብረት ለሚመለከተው ክፍል በባህር መዝገብ ካሰፈረ እና መለያ የባህር መዝገብ ቁጥር ከሰጠ በኃላ ለክፍሉ ያስረክባል።