የአብርሃምን ምድብ ከፊደል ቆጠራ እስከ ማንበብ እንዲሁም ከትምህርተ ሃይማኖት ጀምሮ ምሥጢራትን በማስተማር ላይ ይገኛል በተጨማሪም በመዝሙር አገልግሎት ከሰንበት ትምህርት ቤቱ መዝሙር ክፍል ጋር በመቃላቀል በመዝሙር በማገልገል ላይ ይገኛሉ፤ ከአብርሃም ቀጥሎ ያለው ምድብ የይስሐቅና የያዕቆብ ምድብ ሲሆን ሕፃናቶቹን ፊደል ማስቆጠርና በቃላቸው ፊደላቱን እንዲያውቁና እንዲጽፉ በተጨማሪም መዝሙር በኦንላይን እየተላከላቸው አጥንተው መልሰው በመላክ እርማት እየተሰጣቸው አገልግሎት ያቀርባሉ፤ የግዕዝ ትምህርትን ለመላው ለሶስቱም ምድብ ከዚህ በፊት በነበሩት ቀሲስ ሰሎሞን ተጀምሮ ነበር በኦን ላይን በመሀል መምህራን የሥራ ለውጥ ሲያደርጉ በሕፃናቱ መምህራን ቀጥሎ ነበር ከዛ አባታችን አባ በርናባስ ሲመጡ እንደገና በኦን ላይን ቀጠሉልን የኦን ላይኑ ብዙም አጥጋቢ ስላልሆነ በአካል በሳምንት ሶስት ቀን ባዳሩ ያስጠኗቸው ነበር በመሀል አባታችን ሲሳፈሩ ወደ ኦን ላይኑ ተመልሶ በሳምንት ሁለት ቀን ማክሰኞ በሕፃናቱ መምህራን እገዛ ያጠኑና ዓርብ እለት ደግሞ ከአባታችን ያስጠኗቸዋል። ሰኞ እለት በአባታችን አባ ኢዮብ ስለ ቅዱሳን ታሪክ ይማራሉ በድጋሚ በድምፅ ይላክላቸው እና ፈተና ከውስጡ በሕፃናት መምህራኖች ወጥቶ በጽሁፍ ይቀርብላቸው፤ በአካል የምንገናኝባቸው ግዜያት ሰንበተ ክርስቲያን እሁድን ነው ከቅዱስ ቁርባን በኋላ ወጥተው ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ፊት ለፊት እናስኬዳለን።