የአህጉረ ስብከት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይመደብልን ጥያቄን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች :-

0 Comments
1. የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እንዲመሩና እንዲይዙ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
2. የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የከሚሴ የደቡብ ወሎ ልዩ ዞን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ደርበው እንዲመሩ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
3. የምሥራቅ ወለጋንና የሆሮ ጉድሩን ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ጳጳስ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
4. ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ የአሉባቦር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ ወለጋና ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
እነዚህን ውሳኔዎች ሲወስንም ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን በተደራቢ እንዲመሩ የተያዙት አህጉረ ስብከት በዘላቂነት ሊቃነ ጳጳሳት ተመድበው እስከፈታ ድረስ የተወሰነ ውሳኔ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *