የስዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ያዘጋጀው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ።

0 Comments
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚገኙ መንፈሳዊ ኮሌጆች አንጋፋው የብዙ ሊቃውንት ማፍለቂያ የሆነው የስዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለመምህራን እና አስተዳደር ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል።
ሥልጠናውን ከሰጡት መምህራን መካከል አንዱ ፕሮፈሰር አባ ኃይለገብርኤል ግርማ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ በማስተማር ሥነ ዘዴ ( Pedagogical Sciences ) የማስተማር ጽንሰ-ሐሳብ እና ልምምድ እንዲሁም ሥነ ዘዴዎችን ዙሪያ ሥልጠና ተሰጥተዋል ።
በሥልጠናው የማስተማር ሥነ ዘዴ እና ስልቶች ፣ፍልስፍናዎች ፣ የማስተማሪያ ቴክኒኮችን፣ የትምህርት እንቅስቃሴዎችን፣ እና የተማሪን ትኩረት እና ትምህርት ግምገማን ጨምሮ በአስተማሪዎች እና በተማሪዎች መካከል ያለውን መስተጋብር ሂደት ምን መምሰል እንዳለበት ገለጻ አቅርበዋል ።
በሥልጠናው ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ሥነ-ልቦናዊ እድገትን እና መምህራን ተማሪዎችን እንዴት መከታተል እንዳለባቸው የሚያስረዱ ሐሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።
በዕለቱ የተሰጠው ሌላው ሥልጠና በመ/ር ይቅርባይ እንዳለ በተቋማዊ አስተዳደርና አሰሠራር እንዲም ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም በሚል ርዕስ ገለጻ አቅርበዋል ።
በሥልጠናው ውጤት ተኮር ሥራ ለመሥራት በዕቅድ እና ስትራቴጂ አመራር አርአያነት እና መልካም ምሳሌ መሆን አስፈላጊነት ላይ ገለጻ አቅርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
ኮሌጁ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች አቅም ለማጎልበት በበጀት ዓመቱ ተከታታይ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጥ የገለጹት የኮሌጁ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ በኩረ ሰላም ብርሃኑ ሻረው ኮሌጁ ባለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 17 መማሪያ ክፍሎች የሕንጻ ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ገልጸው ሥልጠናው ኮሌጁ እያከናወነ ያለውን ልማት በሰለጠነ የሰው ኃይል ለማሳደግ ወሳኝ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *