የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮለጅ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በሕጻናትና ወጣቶች ላይ በተለይም በሴቶች ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛት ለማስቀረት ለኮሌጁ ማኅበረሰብ እና ለደቀ መዛሙርት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል።
ሥልጠናው በሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት አስተባባሪነት እየተሰጠ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካ ቤንች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ; ፣ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ፣
ሊቀ ኀሩያን ሰርፀ አበበ የኮሌጁ ዲን ;መ/ር ይቅርባይ እንዳለ የሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት ዋና ሥራ አሥኪያጅ የኮሌጁ ሠራተኞችና ደቀመዛሙርት በተገኙበት ሥልጠናው ተሰጥቷል ።
በኩረ ሰላም ብርሃኑ ሻረው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ኮሌጁ በቀጣይም ለመምህራንን እና የኮሌጁ ደቀመዛሙርት በተለያዩ ጉዳዮች ሥልጠና ለመስጠት በሰፊው እየሠራ መሆኑን ገልጸው ለሥልጠናው ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመስግነዋል ።