የዕቅድና ልማት ክፍል

የደብረ ሲና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰ/ጉ/የዕቅድና ልማት ክፍል ሥራ ዝርዝር የሚያሳይ ሠንጠረዥ

ተ.ቁየሥራው መደብየሥራ ዝርዝርምርመራ
1ዕቅድና ልማት ክፍልየአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊጊ ዕቅድ በማውጣት ልዩ ልዩ የሥራ ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ፤ የዕቃ፤ የዕውቀትና የጉልበት ርዳታና መዋጮ ከምእመናን፤ ከልዩ ልዩ ድርጅቶች ሊገኝ የሚችልበትን ሁኔታ እያጠና ለሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡ 
ለአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን የገቢ ምንጭ የሚገኝበትን ተስማሚ የሥራ መስክ ያዘጋጃል፤ ለንዋየ ቅድሳት፤ ለመጻሕፍት፤ ለአልባሳትና ለሌላም የቤተ ክርስቲን አገልግሎት የሚውልና ለገቢ ማስገኛ የሚሆን የቅርጻ ቅርጽና የተግባረ ዕድ ሥራ እንዲቋቋም ያስደርጋል፡፡ 
በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን የሚገኙት ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችም ያላቸውን ዕውቀት፣ የጥሬ ገንዘብ ሀብት ልዩ ልዩ ዕቃዎችና የሰውን ጉልበት ጭምር በማስተባበር ለቤተ ክርስቲያኑ ልማት ሥራ እንዲውል ያስደርጋል፡፡ 
ካህናት በትርፍ ጊዜያቸው ራሳቸውን ለመርዳት እንዲችሉ የገቢ ምንጭ ለማስገኘት የሚመለከታቸውን በማስተባበር ከቤተ ክርስቲያኑ አገልጋዮች መካከል እየሠለጠኑ በየዝንባሌያቸው እንዲሠማሩና የምርት ውጤት እንዲያስገኙ ያስደርጋል፡፡ 
ከልማቱ የሚገኘው ገቢ በሰበካ ጉባኤው ካርኒ እየተሰበሰበና በገንዘብ ቤቱ እየተጠቃለለ በቤተ ክርስቲያኑ ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ገቢ ይሆናል፡፡ 
የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ቦታዎች እንዲለሙ እያጠናና እያስጠና ተግባራዊ እንዲሆን ለሰበካ ጉባኤው ያቀርባል፡፡ 
የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ የይዞታ ቦታዎች ከመመሪያ ውጭ የበላይ አካል ሳይፈቅድ ለሦስተኛ ወገን እንዳይሰጡ ይቆጣጠራል፤ ይከታተላል፡፡ 
የሥራውንም ውጤት በሚመለከት በየሦስት ወር ለሰበካ ጉባኤው ሪፖርት ያቀርባል፡፡