በዋናነት ተሰርተው ያለቁ/ የፀደቁ ነገሮች እንዳለ ሆነው ሁለተኛ ደረጃ ሲቀጥል እየተሰሩ ያሉ ነገሮች በዋነኝነት ስናስቀምጣቸው ከሥነ ሥርዓት ክፍሉ ካሉት 28/አባላት መካከል 4 ልጆችን በአመራርነት፣ በመምረጥ ስራውንበጥሩሁኔታ፣ እያካሄደ ይገኛል እነሱም
- በጸሐፊነት
- በንብረት ክፍል
- በቁጥጥር ክፍል
- በፅዳት ክፍል
- በአቴዳንስ ክፍል መርጦ እያሠራ ነው፣
- በየወሩ ስብሰባ እያካሄደ የአገልግሎቱን ሁኔታ ያጤናል ይገመግማል /አጀንዳ ይሰጣል
- በየሳምንቱ ከክፍሉ /7/ልጆችን እየመደበ ከመዝሙር ክፍልም ደግሞ፣11 ልጆችን እየመደበ አብሮ በመከታተል ይሠራል
- በአገልግሎት መካከል ክፍተት ካለ ስህተት ካለ ቅሬታ ካለ በራሱ ከስብሰባ ውጪ በሥነ ሥርዓት ክፍሉ ባለው ቡድኑ ውስጥ በኦላይን አቀራርቦ ነገሮችን ያስማማል ያግባባል፤ ቅሬታውን እንዲፈታ ያደርጋል።
- የተለያዩ ጥቃቅንና ትናንትሽ ለአገልግሎት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በራሱም ሆነ በግልም በመዋጮም በጀት መድቦ የሚያስፈልገውን ነገር ገዝቶ ያሟላል፤
- በየሳምንቱ ያለማቋረጥ በሶስቱም የመዝሙር ምድብ በስምም፣ ሆነ በቁጥርም አስተካክሎ አቴዳንስ በሳምንትና፣በየ15 ቀኑ እሚመጡትን እና ያሉትን፣ እያየ የሌሉት፣ እህቶችን ደግሞ እየተከታተለ፣ እየጠየቀ አቴዳንት ይይዛል
- ዐበይት በዓላት ባሉ ሰአት ሙሉ የክፍሉ አባል ከአዳር ዋዜማ ጀምሮ እስከ ጠዋት እስከ ምሽት ደረስ ቆሞ ያገለግላል በሚችለው አቅም
- መስተንግዶዎች በሌሉ ሰአትና ጊዜ በፍላጎት እና በቅንነት ለማስተናገድ ለሚመጡ እህቶች ሥነ ስርዓት ክፍሉ በራሱ ነጭ በነጭ አልባሳትን በማዘጋጀት አገልግሎቱ እንዲቀጥል ያደርጋል
- ሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ ካሉ ከ7 ክፍሎች ጋራ ከ6 በሚያሰፈልገው ነገር በጋራ ይሰራል /
- ሥነ ሥርዓት ክፍሉ ከበላይ አመራር አካላት ስብሰባ ባለው ሰአት ከላይ ለሚመጣው ጥያቄም ሆነ ትእዛዝ መልስ በመስጠትይሰራል
- በየጊዜው አባላትን በመምረጥ ወደ ክፍሉ ያሰገባል አገልግሎቱ ሰፋ እንዲል እንደ አጠቃላይ ከብዙ በጥቂቱ በነዚህ ሶስት አመታት ሥነ ሥርዓት ክፍሉ በእነዚና የመሳሰሉት ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡