
በሥርወ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት የትምህርት ክፍሉ አገልግሎት
በሥ/ሃ/ሰ/ት/ቤት/ግንኙት ክፍል የሚሠሩ የሥራ ዝርዝር
የሥርወ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት የንብረት ክፍል የስራ ድርሻ
በንብረት ክፍላችን ______አባላት በንዑስ ክፍልነት ያሉን ሲሆን የስራ ድርሻችንም እንደሚከተለው ነው:-
1. በንብረት ክፍል ስር የሚገኙ ንብረቶችን በተዘጋጀላቸው የንብረት ቅጽ ላይ መዝግቦ በመያዝ በአይነታቸው ለይቶ በአግባቡ መጠበቅ እንዲሁም ብልሽቶች እንዳይደርስባቸው መጠበቅ።
2. በተለያየ ግዜ በግዢም ሆነ በስጦታ ወደ ክፍሉ የሚገቡ አዳዲስ ንብረቶችን እየተረከበ በንብረት መረከቢያ ቅጽ ላይ በመመዝገብ በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ።
3. በክፍሉ ውስጥ ከሚገኙ ንብረቶች መካከል በውሰት የሚወጡና የማይወጡ ንብረቶችን ይለያል።
4. ለአገልግሎት በውሰት የሚወጡ ንብረቶችን የማዋሻ ቅፆችን በማዘጋጀት በቅፁ ላይ እየመዘገበ ይሰጣል ያውሳል። የተዋሱትን ንብረቶች በተፈቀደላቸው የግዜ ገደብ ውስጥ መመለሳቸውን ይከታተላል ያልተመለሱ እንዲመለሱ ያድርግልን
5. በተለያየ ሁኔታ ከክፍሉ የጓደሉ (የጠፉ) የተበላሹ የሚጠገኑበትን የሚተኩበትን መንገድ ያመቻቻል ለክፍሉ አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑ የመገልገያ መሳሪያዎች እንዲሟሉ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር የበኩሉን አስተዋፅኦ ያደርጋል።
6. በንብረት ክፍሉ ስር የሚገኙ ንብረቶችን የሰ/ት/ቤቱ መሆናቸውን የሚያመለክቱ መለያ ምልክት እንዲኖር ያደርጋል።
7. ቢበዛ ሁለቴ ካነሰ አንድ ግዜ በዓመት ውስጥ የየክፍሉን ንብረቶች ቆጠራ ያከናውናል።
8. በተለያየ ግዜ በስጦታም ሆነ በማንኛውም መንገድ ወደ ሰ/ት/ቤታችን የገባውን ንብረት ለሚመለከተው ክፍል በባህር መዝገብ ካሰፈረ እና መለያ የባህር መዝገብ ቁጥር ከሰጠ በኃላ ለክፍሉ ያስረክባል።
በየሳምንቱ እሑድ እሑድ ይቀደሳል። በየወሩ የቅዱስ ሚካኤል፣ የቅዱስ ገብርኤል፣ የቅድስት ድንግል ማርያምና የበዓለ እግዚአብሔር ይቀደሳል። በየዓመቱ ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል ሐምሌ ሥላሴ ነሐሴ 1-16 ጳጉሜን 3 ቅዱስ ሩፋኤል የዘመን መለወጫ መስከረም 1ቀን መስከረም 17 በዓለ መስቀል ኅዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል ታሕሣሥ 19 ቀን ቅዱስ ገብርኤል የልደት በዓል ጥር 11 ቀን በዓለ ጥምቀት የትንሣኤ ግንቦት 1 ቀን የልደታ ሰኔ 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ሀምሌ 5 አቦ ፡፡
Get in Touch 24/7
Square, Ain Aar, Lebanon
God is Good All The Time!
Subscribe to our News,